የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሥሩ የሚገኙ ለመኖሪያ/ ገስት ሀውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የ6ኛ ዙር የመኖሪያ/ገስት ሀውስ ቤቶች ኪራይ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቀጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/12/09/2018

1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሥሩ የሚገኙ ውስጥ ለመኖሪያ/ ገስት ሀውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/12/09/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

2 ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የመኖሪያ/ ገስት ሀውስ ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሠረት ነው።

4. ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ቅዳሜን ጨምር ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን ለገሐር በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢ አደራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ወይም ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺሕ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ጨረታው ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለጸበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ሥራ በሚመደቡ ባለሙያዎችና በሚወጣው ፕሮግራም መሠረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።

7 ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 09 10-18-59-48/ 09 22-49-18-85 ወይም 09 22-98-76 33 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዌብሳይት/ website www.fhe.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ. PO Box 299

ፋክስ ቁጥር፡ 011-554-6015 / 011-552-1616

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-06-29 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Housing Corporation
  • Bid bond: 25,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 09, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T08:28:52.000Z
  • Buyer website: https://www.fhc.gov.et

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders