የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ካስገነባቸው ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን ማከራየት ይፈልጋል
Description
የ8ኛ ዙር የመኖሪያ/ገስት ሀውስ ቤቶች የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/11/11/2018
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ካስገነባቸው ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በወጪ ምንዛሬ ተመን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/11/11/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የመኖሪያ /ገስት ሃውስ ቤቶች ክራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው።
4. ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከሐምሌ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 1000 አንድ ሺህ ብር በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰበሰቢያ አደራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ወይም ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 50000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መስረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0910-48-59-48 ወይም 0922-9876-33 ወይም 0922-49-18-85 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et
የፖ.ሣ.ቁ. PO. Box 299
ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46-46
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-07-21
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-07-21 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: Jul 10, 2026
- Posted at: 2026-07-10T07:25:01.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.