በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሲስተም ሶፍትዌሮችን እና ሰርቨር ኮምፒዩተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የገዥ መለያ ቁጥር ፡ አብክመ/ኢቴቢ/ግ/ጨ/07/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሲስተም ሶፍትዌሮችን እና ሰርቨር ኮምፒዩተሮችን ማለትም ፡-
- ሎት 1- Digital Finance information Management System
- ሎት 2 Server Computers በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ስፔሲፊኬሽን ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚለሙ ሶፍትዌሮችን እና ሰርቨር ኮምፒዩተሮችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ |ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በተቋሙ ዋ/ገንዘብ ያዥ ቢ/ቁ/02 በመምጣትና የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን የሲስተም ልማትና ሰርቨር ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን፣ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የፋይናንሻል (የዋጋ) ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሌላ ፖስታ በማድረግ ለየብቻ በታሸጉ 2 ፖስታዎች (ቴክኒካልና ፋይናንሻል በማለት) ጨረታው በአዲስ ዘመመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡30 ጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው የሚለየው በሎት (ምድብ) ዋጋ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በቴክኒካል ሰነዳቸውና በፋይናንሻል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግይጠበቅባቸዋል፡፡ ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583206856 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-22 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 08, 2026
- Posted at: 2026-06-09T08:49:21.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.