የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለሁሉም የዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለሁሉም የዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ 

  • ሎት 1 የመኪና ሞተር ዘይት እና ቅባት፣ 
  • ሎት 2 የመኪና ጎማ፣
  • ሎት 3 ፋስት ሞቪንግ የመኪና እቃዎች
  • ሎት 4 የመኪና እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት በጨረታው መወዳደር ለምትፈልጉ አካላት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin Number ያላቸው፣

3. የግዥ መጠኑ 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና ከዚያ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT የተመዘገቡ መሆናቸውን ሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ | ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣ ተጫራቶች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ተያይዞ መታሸግ አለበት።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ።

8. አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።

9. ውድድሩ የሚካሄደው በእቃዎቹ አይነት በሎት በጠቅላላ ድምር ዋጋ ነው።

10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

11. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል።

12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 610 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር  033 111 8118/ 19 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው አካል ያሸነፈውን ንብረት ደቡብ ወሎ ዞን በሁሉም ንብረት ክፍሎች ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።

የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-24 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: South Wollo Zone Finance Command
  • Bid bond: 1.5%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 09, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T08:53:24.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders