ብርሃንና ሰላም ማተሚያ የመነፅር ሥራ አገልገሎት ግዥ፣ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች ፍተሻ፣ ሙሌትና የመለዋወጫ አቅርቦት አገለግሎት ግዥ፣ ካርቦን (HAND CARBON) በጨረታ አወዳድሮ በመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 015/18

ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ በመግዛት ይፈልጋል።

  • በጨረታ አንድ (ሎት 1)፦ ለሁለት ዓመት የሚቆይ የመነፅር ሥራ አገልገሎት ግዥ፣
  • በጨረታ ሁለት (ሎት 2)፦ ለሁለት ዓመት የሚቆይ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች ፍተሻ፣ ሙሌትና የመለዋወጫ አቅርቦት አገለግሎት ግዥ፣
  • በጨረታ ሶስት (ሎት 3)፦ ካርቦን (HAND CARBON) ብዛት 150 ፓኬት ግዥ፣

ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመስስ ብር 300.00 ከፍሎ በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።

ጨረታው 30/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለጹ በቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶከመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።

ስልክ ቁጥር 011-155-5280 ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)

Berhanena selam printing enterprise

አዲስ አበባ

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-07 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhanena Selam Printing Enterprise
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 09, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T08:58:44.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders