የአምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተ. ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ መጋዘን ያከማቸውን እህል በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የእህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የአምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ. የተ. ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ መጋዘን ያከማቸውን ነጭ ጤፍ 2,774 + ኩንታል ሠርገኛ ጤፍ 1,350 + ኩንታል ቀይ ጤፍ 517 + በጠቅላላው 4,641 + ኩንታል በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ነገሮች

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከዩኒየኑ ገበያ መምሪያ በብር 1000.00 መግዛት ይችላሉ።
  2. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች አህሎቹ ያሉበትን ሁኔታ አምቦ ከተማ በሚገኛው የዩኒየኑ መጋዘን በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ወዲያው የሚመለስላቸው ይሆናል።
  5. ጨረታው ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመንጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ17ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በዛው ቀን ጠዋት በ 5፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል። 17ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥላው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ በሰዓቱ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠየቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም። እንዲሁም ተጫራቹ  ጨረታውን በአንዱ የእህል ዓይነት ወይም በሁሉም የእህል ዓይነት ላይ መጫረት ይችላል።
  9. ጨረታውን ያሸናፈ አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ የጠቅላለውን ግዥ ዋጋ ባስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ላይ 5% ለዋስትና በባንክ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  10. ዩኒየኑ ለእህሉ ሽያጭ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 260 9101 ወይም 011 236 3399 ይጠቀሙ።

አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተወሰነ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-26
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመንጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ17ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ጠዋት
  • Bid opening: 2026-06-26 11:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመንጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ17ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት ጠዋት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ambo Farmer's Cooperative Union
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published: Jun 10, 2026
  • Posted at: 2026-06-10T08:13:10.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders