የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ዋና መስሪያ ቤት) የሚገኙ የሽያጭ ማሽኖች የጥገና እና የማሻሻያ (ማዘመን) (Bid for Vending Machine Repair and Upgrade) ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: - SSNT-T615

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ዋና መስሪያ ቤት) የሚገኙ የሽያጭ ማሽኖች የጥገና እና የማሻሻያ (ማዘመን) (Bid for Vending Machine Repair and Upgrade) ስራዎችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ለሆኑ ብቁ የአገልግሎት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  1. በሽያጭ ማሽኖች የጥገና ፤ የማሻሻያ (ማዘመን) እና ተዛማጅ አገልግሎቶች ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራፈቃድ ፤ የግብር ከፋይ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሀምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT -T615 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስምና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ” ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ሀምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይምወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

አሸብር ተሾመ በስልክ ቁጥር፡ +251-11 517-4918 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ኢ.ሜ.ል:- ashebirte@ethiopianairlines.com 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Ethiopian


Tender details

  • Deadline: 2026-07-13
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-07-13 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 100 ብር
  • Published: Jun 10, 2026
  • Posted at: 2026-06-10T08:28:30.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders