ፀደይ ባንክ አ.ማ. በብዛት 3 ሱዙኪ ዲዛየር (Suzuki Dzire) መኪኖችን ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0017/2018

ፀደይ ባንክ አ.ማ በብዛት 3 ሱዙኪ ዲዛየር (Suzuki Dzire) መኪኖችን ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።

1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ በጨረታ ለመካፈል /ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ/ ሊኖራቸዉ ይገባል።

2. ተወዳዳሪዎች መኪኖቹን የሚያከራዩበትን ዋጋ በጨረታ ዶክመንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ለጨረታ ማስከበሪያ የሶስቱን መኪኖች የአንድ ወር አጠቃላይ የክራይ ዋጋውን 2% በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ የ90ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡ ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።

4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አንድ መቶ ብር /100.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

6. የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።

7. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0115 581 658

ፀደይ ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-24 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 10, 2026
  • Posted at: 2026-06-10T09:02:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders