በባሌ ዞን የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል በ2017 በጋ ወቅት ያመረታቸውን የተለያዩ የስንዴ ዝርያ ብዛት በኩንታል 287.95 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሰባት ከ 95/100 ኩንታል) በማሽን ተበጥረው ንፁህ ለምግብና ለፋብሪካ የሚውሉ የተለያዩ የፓስታ እና የማካሮኒ ስንዴ ዝርያ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በባሌ ዞን የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል በ2017 በጋ ወቅት ያመረታቸውን የተለያዩ የስንዴ ዝርያ ብዛት በኩንታል 287.95 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሰባት ከ 95/100 ኩንታል) በማሽን ተበጥረው ንፁህ ለምግብና ለፋብሪካ የሚውሉ የተለያዩ የፓስታ እና የማካሮኒ ስንዴ ዝርያ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ባለቤቶች ፣ መንግሥታዊ ወይም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ግለሰብ ነጋዴዎች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) Oromia Agricultural Research institute internal revenue B ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000466928357 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማስገባት ሰነዱን ከባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 15 መግዛት የሚችሉ ሲሆን ፤ ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የስንዴ ዝርያዎች ዓይነት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20% (20 ፕርሰንት) የያዘ ሲፒኦ ብቻ የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱበን ሰነድ በመግዛት 1ኛ. ኦርጅናል የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላባት) ሰነድ & 2ኛ, ዋጋ የተሞላባት ኮፒ ሰነድ የሁለቱንም ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት እለት እና ሰአት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ላይ የድርጅታቸውን ወይም የግለሰቡን/የነጋዴውን ስም እና ሙሉ አድራሻ ስልክ ቁጥር በመፃፍ መፈረም ይኖርባቸዋል ።
4. ተጫራቾች የሚሸጡትን የስንዴ ዝርያዎች ናሙና በባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 ወይም በማዕከሉ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
5. በተጫራች የመወዳደሪያ ዋጋ የሚሞላው ስርዝና ድልዝ የሌለውና በግልፅ የሚነበብ መሆን አለበት።
6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል ስም ያስያዙትን ሲፒኦ ኦርጅናል የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላባት ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. በእያንዳንዱ የመወዳደሪያ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት።
8. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁትር 15 ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል ስንዴውን መረከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
በባሌ ዞን የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-25 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Bale Zone Sinana Agriculture Research Institute
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 10, 2026
- Posted at: 2026-06-10T10:02:40.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.