የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጎማና ባትሪ፣ የመኪና ጌጣጌጥና አልባሳት እንዲሁም ለመኪና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ ብ.ግ.ጨ/ዕግ/44/10/2018
1.የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
- የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጎማና ባትሪ የመኪና ጌጣጌጥና አልባሳት እንዲሁም
- ለመኪና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ
- የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ./ብ.ግ.ጨ/ዕግ/44/10/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚፈጽመው የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጎማና ባትሪ የመኪና ጌጣጌጥና አልባሳት እንዲሁም ለመኪና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን እና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይኸንን አስመልክቶ መመሪያ ቁጥር 1070/2017 በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በቀድሞ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሁለተኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ወይም ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ጋራንት በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
ሎት |
የሰነድ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
ሎት 1 |
የተሸከርካሪ መለዋወጫ |
40,000.00 |
|
ሎት 2 |
የመኪና ጎማና ባትሪ የመኪና ጌጣጌጥና አልባሳት |
30,000.00 |
|
ሎት 3 |
ለመኪና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ |
20,000.00 |
6. ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፣ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከተር 2ኛ ፎቅ ይከፈታል።
7. በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች በኮርፖሬሽኑ በግንባር በመገኘት ዕቃውን ያስረክባል።
8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-855 36-17 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-25 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 11, 2026
- Posted at: 2026-06-11T07:55:26.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.