የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ሊያሠራ ላቀደው የፋርማሲ ብሎክ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ሊያሠራ ላቀደው የፋርማሲ ብሎክ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፦

1. ደረጃቸው GC 5/BC 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2018 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን  ባለሥልጣን ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።

2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።

3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ሕጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መሥሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።

4. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትከክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

5. የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

6 የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፊቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።

8. የጨረታው ሰንድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል ፋይናንስ ከፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያዉ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።

10. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Publishing entity: Leku General Hospital
  • Bid bond: 120,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 11, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders