በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ እቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 31/2018 ዓ.ም

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ እቃዎች፣ dorco/ምላጭ/፣ Mosquito net /አጎበር/፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ በግልፅ እንዲሁም Hair clipper/ቶንዶስ/፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማ፣ welding electrod፣ dorco/ ምላጭ/ እና Woven bag በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-

1) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም እድሜው ከ-18-አመት በላይ የሆነ የኗሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።

2) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል።

3) የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም።

4) በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

5) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 03፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።

6) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።

7) የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።

8) ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተሰጠው የጊዜገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።

9) ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል።

10) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።

11) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

12) መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 0693 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-06-17 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 11, 2026
  • Posted at: 2026-06-11T08:46:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders