የኢትዮጵያ ብቃትና ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት አዲስ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 027/18
የኢትዮጵያ ብቃትና ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት አዲስ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል.
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 10፡30 የማይመለስ 500 / አምስት መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመከፈል ደረሰኝ ይዘው በአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 208 በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
3. የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽገው ማቅረብ አለባቸው፣
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን 200,000.00 ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ21ኛው ቀን 8፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ9፡00 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
7. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09
ስልክ ቁጥር 011 645 4147 / 011 645 3598 / 011 869 4931 / 09 94 11 55 13 ከመገናኛ አያት 49 መንገድ ከሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ብቃትና ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ21ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-01 15:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ21ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Management Institute (EMI)
- Buyer address: ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jun 11, 2026
- Posted at: 2026-06-11T08:49:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.