የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጊቤ 3ኛ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሰራተኞች ላስገነባው የመኖሪያ ህንጻ ቋሚ እና አላቂ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/06/2018
1. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጊቤ 3ኛ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሰራተኞች ላስገነባው የመኖሪያ ህንጻ ቋሚ እና አላቂ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEP Transmission Substation Construction አካውንት ቁጥር 1000252665203 ገቢ በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ትሪዠሪ አስተዳደር ቢሮ ደረሰኙን በማስመራት የጨረታ ሰነዱን ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን ቋሚ እና አላቂ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/06/2018 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ለ90 (ዘጠና) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።
6. ጨረታው ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ጄነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ይከፈታል።
7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-557 4011 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-06-22 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Power
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: Jun 12, 2026
- Posted at: 2026-06-12T07:14:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.