የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር APPC 004/18
በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት በኮሌጁ ለሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች መገልገያ እና በአመቱ በተለያዩ ወቅት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ለሰልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ።
- ሎት 1 የምግብ እህሎች ፣ ጥራጥሬዎች እና አትክልቶች
- ሎት 2 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 3 የተለያዩ የፅዳት እቃዎች ፤
- ሎት 4 ልዩ ልዩ አልባሳቶች፤
- ሎት 5 የተለያዩ ቋሚ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤
- ሎት 7 የባህር ዛፍ ማገዶ እንጨት ፤
- ሎት 8 የበሬ ስጋ ለወጥ የሚሆን ምንም አይነት አጥንት የሌለው ፤ ግዥ በማስፈለጉ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዚህ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
ጨረታው የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥ አዋጅ በተገለፀው ግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት መሰረት ይፈጸማል፣ የምግብ እህሎች ፣ ጥራጥሬዎች እና አትክልቶች የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች ፤ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ አልባሳቶች፣ የተለያዩ ቋሚ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የጥገና የቧንቡውሃ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች ፤ የባህር ዛፍ ማገዶ እንጨት እና የበሬ ስጋ ለወጥ የሚሆን ምንም አይነት አጥንት የሌለው ጨረታው የሚያከናውነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በ2019 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ወቅታዊ ደብዳቤ / Tax clearance / ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም ተ.እ.ታ / VAl / ሰርተፊኬት እና ቲን / TIN / ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል በሁሉም ሎቶች ላይ የሚወዳደሩ አቅራቢዎች የሚያቀርቡት ሰነድ በአጠቃላይ የታደሰ መሆን አለበት።
ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የኢትዩጰያ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር / ከፍለው የጨረታውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 28 በስራ ቀናት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ በአነስተኛ እና ጠወቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበት የህጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል፡፡ ከአደራጃቸው አካል በሚጫረቱበት ሎት በዘርፉ መሰማራታቸውን የሚገልፅ የቅርብ ጊዜ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው ፤
ተጫራቾች በሎት 1 ብር 10,000.00 / አስር ሺህ ብር /፣ በሎት 2. ብር 10,000.00 / አስር ሺህ ብር / ፤ በሎት 3. ብር 10,000.00 / አስር ሺህ ብር / ፧ በሎት 4. ብር 15,000.00 / አስራ አምስት ሺህ ብር / ፣ በሎት 5. ብር 30,000.00 / ሰላሳ ሺህ ብር / ፧ በሎት 6. ብር 15,000.00 / አስራ አምስት ሺህ ብር / ፤ በሎት 7. ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር / እና በሎት 8. ብር 20,000.00 / ሃያ ሺህ ብር / የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲ.ፒ.ኦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ስም አዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 ቀናት ቅዳሜ ፣ እሁድን እንዲሁም የበዓል ቀናትን ጨምሮ በኮሌጁ ፋይናንስና ግዥ ዲቪዚዮን በመቅረብ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሁለት ፖስታ ፋይናንሺያል ኮፒና ኦሪጂናል እንዲሁም በሁለት ፖስታ ቴክኒካል ኮፒና ኦሪጂናል በድምሩ በ4 ፖስታ ሰነዶችን በመለየት ማስገባት አለባቸው።
ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፤ የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል የመዝጊያውና የመክፈቻው ቀን የመንግስት ስራ ቀን ወይም ካላንደር / የቀን መቁጠሪያ / የሚዘጋው በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይሆናል።
ተጫራቾች በሚጫረቱበት ሎት ላይ በግምጃ ቤታቸው በቂ የሆነ የእቃዎች ከምችት መኖር አለበት።
ሌሎች ደጋፊ ሰነዶችን እንደ የመልካም ስራ አፈፃፀም እና የመሳሰሉትን ማቅረብ የተሻለ ውጤት አለው፤
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ኮልፌ ሉኳንዳ አዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ማሰልጠኛ ማዕከል / የቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ / አጠገብ።
ለበለጠ መረጃ 0112-73 -94-86፤ 0112-73-95-48 ወይም 251-118-33-38-45
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-22 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Police Commission
- Buyer address: ኮልፌ ቀራዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ምሪያ ከጦርኃይሎች በስተግራ ቀለበት መንገድ ሲወርዱ የቀድሞው ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ሳይደርሱ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300 (ሶስት መቶ ብር)
- Published: Jun 12, 2026
- Posted at: 2026-06-12T07:30:30.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.