ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪዎች ጎማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዕ.ደ.ት.ድ ግዢ 009/18

የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማዎች ግዥ ግልፅ ጨረታ መመሪያ ድርጅታችን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-

1. ተጫራች የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርበታል፤

2. ተጫራች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች አቅርቦት ስለመፈጸሙ የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ ቤት ከፋይናንስ ሂ/ደ/የስ/ሂ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፤

4. ተጫራቾች ከዚህ ደብዳቤ ጋር በአባሪነት በቀረበው የሥራ ዝርዝር ላይ የሚወዳደርበትን ዋጋ ነጠላ ዋጋ (unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total Price) በግልፅ አሃዞችን በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት ይህ የጨረታ ጥሪ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስተጫራቾች ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል ፣ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፣ፋይናሺያል ኦርጅናል ፣ፋይናንሺያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በግዢ ዲፓርትመንት ዳይክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤በዚሁም ዕለት ከቀኑ 8፡30 ጨረታ ይከፈታል።

5. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ናሙና ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

6. ተጫራቾች የፋይናንሺያል ሰነድ 30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

7. የቴክኒክ ግምገማ ውጤት 70/100 ወይም 51/70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለፋይናሺያል ውድድር ግምገማ ያልፋሉ፡፡ በፋይናንሺያል ግምገማ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተጫራቾች አሸናፊ ይሆናሉ።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ የመወዳደሪያ ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል፤

9. በተጫራች የሚቀርብ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፤

10, ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጡት ዋጋ መለወጥ ሆነ ማሻሻል አይችሉም፤

11.ማንኛውም ተጫራች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፤

12. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለምን ያህል ጊዜ እንዲሚቆይ በጨረታው ሰነድ ላይ መግለፅ አለባቸው፤

13. ተጫራቾች በሠንጠረዥ ላይ የተመለከተውን የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማዎች በመጥቀስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የሚጫረቱበትን የእያንዳንዱ ሎት፤ ለተለያየ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ተጫራጭ ውጤቱ በፁሁፍ እንደተገለፀለት በ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ውስጥ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና (ፐርፎርማንስ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ በማስያዝ በግንባር ቀርበው የተዘጋጀውን ውል በመፈረም በ15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ንብረት ሙሉ አቅርቦት መፈጸም ይኖርበታል፤

15.ተጫራች የተለያየ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች የዋጋ ማቅረቢያ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርበታል፤

16. አሸናፊ ተጫራች የተበላሸ የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪዎ ጎማዎች የማስተካከል የመቀየር ግዴታ ይኖርባታል፤

17. አሸናፊ ተጫራች የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች በሙሉ ዋና መ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፤

18. አሸናፊ ተጫራች በገባው ውል መሰረት በ15 ቀናት ውስጥ ንብረቶችን ባያስረከረብ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤

19. ያላሸነፉ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ውጤቱ እንደተገለፀ ወዲያውኑ 100% ገንዘብ ተመላሽ ይደረግለታል፤

20. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤

21. ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሸናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሳይቀየር ብዛት በ20% ለመጨመር ለመቀነስ መብት አለው፤

22. ተጫራቾች የጨረታው ስነ-ስርዓት ከመጀመሩ በፊት ስለጨረታው ሂደትና ከጨረታው ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን በማንሳት ጥያቄ ማቅረብ መብታቸው ሲሆን፣ የጨረታ ስርዓት ከተጀመረ በኋላ የጨረታውን ሂደት ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ሆነው ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳል፤

23. ድርጅቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-

በስልክ ቁጥር 011 4 39 00 75/35 92/15 69/011 439 10 27
ፋክስ 011 439 63 36/0114 74 71 41ፖ.ሳ.ቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- ቃሊቲ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት 70 ሜትር ገባ ብሎ

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-21
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00
  • Bid opening: 2026-06-21 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Elet Derash Relief Transport Enterprise
  • Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንፃ ጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: የእያንዳንዱ ሎት 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 12, 2026
  • Posted at: 2026-06-12T08:07:47.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders