የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የህትመት ዓይነቶችን ለማሳተም ይፈልጋል

Description

የተለያዩ ህትመቶችን ለማሳተም የወጣ የጨረታ
ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/18/2018

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የህትመት ዓይነቶችን ለማሳተም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት የህትመት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ፈቃድ፣ ቫት ተመዝጋቢነት፣ ቲን፣ EGP (የአቅራቢ ተመዝጋቢነት) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ ኤማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ከኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር እንዲሁም ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሽያል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ ቁጥር+251911984467 ወይም +251910567578
ፋክስ፡-0114-421312
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-23 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
  • Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
  • Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 12, 2026
  • Posted at: 2026-06-12T08:20:26.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders