የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከሐምሌ 01/2018 እስከ ህዳር 30/2019 ድረስ ለ5 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም ጥሬ እህል፣ የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከሐምሌ 01/2018 እስከ ህዳር 30/2019 ድረስ ለ5 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም ጥሬ እህል። የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማህበራትም ሆነ ግለሰብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 10.ተጫራ መመሪያ ማሟላት አለባቸው።
1. በንግድ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት። የግብር ከፋይነት (TIN NO ) ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የቫት ከፋይነት እንዲሁም የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ።
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የህግ ታራሚዎች ኮሚቴ የማረሚያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ እና ከዞኑ አቃቢ ህግ ቢሮ እንዲሁም ከዞኑ ገ/ኢ/ትብብር በሚወከሉ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስሪያቤቱ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
5. በበሰለ ምግብ አቅርቦት በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
6. ጥሬ እህል ለማቅረብ ለሚወዳደሩ የእህሉን ናሙና እና የሚወዳደሩበትን አይነት ማቅረብ 16 ይጠበቅባቸዋል።
7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታው ያቀረቡትን ሀሳብ መቀየር ወይንም ማሻሻል ስ! እንዲሁም ከጨረታው እራስን ማግለል አይችሉም።
8. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት አንስቶ በ3 ቀን ውስጥ ማረሚያ ቤት በመቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ ጥራቱን የጠበቀና ለአንድ ሰው የሚሆን ማረሚያ ቤቱ ባወጣው ሜኑ መሰረት አቅርቦት መመገብ አለበት።
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማረሚያ ቤት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳይን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
11. ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውና የውል ማስከበሪያ በጥቃቅንና አነስተኛ ደንብ 192/2009 ተሻሽሎ በወጣው አንቀፅ 27 መሰረት ከአደራጀው ክፍል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው
12. ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል ። ለውል ማስከበሪያ 10% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
13. ምግቡ የሚዘጋጀው በመስሪያቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሆኖ ለማብሰያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች የማረሚያ ቤቱ እንዳለ ሆኖ የጎደለውን ጨረታውን ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ ማሟላት ግዴታ አለበት።
14.ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
15. ተጫራቾች በጫረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ለማ/ቤቱ ለበላይ አካሎች ጨታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 5 ቀን ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ ይችላል።
16 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ የደ/ም/ሸ/ዞን/ገ/ኢ/ልማት/ትብብር ፅ/ቤት ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 011-341-1190 / 011 341-0023
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-30 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: South West Shewa Zone Prison Department
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Jun 12, 2026
- Posted at: 2026-06-12T08:34:13.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.