Amharic

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በማረቆ ልዩ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ሽርንቶ 01 ቀበሌ የጤና ኬላ ግንባታ በተራዶ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 4 /2018ዓ.ም

ሎት 1 የጤና ኬላ ግንባታ

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በማረቆ ልዩ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ሽርንቶ 01 ቀበሌ የጤና ኬላ ግንባታ በተራዶ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር ያላቸው)
  4. ከላይ የተጠቀሰው የመጫረቻ ሃሳብ እንዳለ ሆኖ የጨረታው ቢል ኦፍ ኳኒቲቲ ባለው መጠይቅ መሰረት መረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  5. ተጫራቾች ላለው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመክፈል ከግዥ/ን/ አስ/ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  6. ማንኛውም ተጫራች በማረቆ ልዩ ወረዳ የሚያሳይ CPO ወይም ህጋዊ የባንክ ማረጋገጫ ያለው የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 የሚያሳይ አብሮ ከጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
  7. ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው ለ 21 ተከታታይ ቀናት በማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ባለው ግዥን አስ/ ስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  8.  ጨረታው ከወጣበት በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ግዥ/ን/አ/ ቢሮ ቁጥር 5 በይፋ ይከፈታል።
  9. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት የማረቆ ልዩ ወረዳ

ጤና ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-02
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-02 11:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Mareko Special District Health Office
  • Bid bond: 50,000 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jun 12, 2026)
  • Posted at: 2026-06-12T09:07:41.000Z
← Back to all tenders