አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሀይብሪድ አውቶሞቢል ባለ 7 መቀመጫ (Hybrid Automobile 7 Seat) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/042/2018 ሀይብሪድ አውቶሞቢል ባለ 7 መቀመጫ (Hybrid Automobile 7 Seat) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡

  1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)፣
  2. በመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
  3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)፣
  5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 0118 21 22 14

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-22
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-22 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Organization
  • Bid bond: 1,000,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 12, 2026
  • Posted at: 2026-06-12T09:10:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders