የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (Production Shade) ቀሪ የግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (SEIDPC) በ2018 በጀት ዓመት በጋሞ ዞን፣ በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ በወዛቃ ቀበሌ ሳይት ላይ የሚገኘውን (Production Shade) ቀሪ የግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

ስለሆነም በግንባታ ዘርፍ የተሠማሩና ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መሥፈርቶች-

1. በዘርፉ ደረጃቸው BG-4 ወይም GC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ ኮንትራክተር ሆነው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድና ሥልጣን ከተሰጠው አካል የተሰጠ የዘመኑ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። በተጨማሪም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማረጋገጫ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (rrevocable Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በሁኔታ ላይ የተመሠረተ የባንክ ዋስትና ተቀባይነት የለውም።

3. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ እና የቪኤቲ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ በማቅረብ፣ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በኮርፖሬሽኑ የባንክ አካውንት (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር፤ 1000607480568) ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በኮርፖሬሽኑ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

4. ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ በፊት የሥራ ቦታውን (Site) በራሱ ወጪ ሄዶ ማየትና ማረጋገጥ ይኖርበታል።

5. በአካባቢው (በክልሉ) ውስጥ በማንኛውም የግንባታ ሥራ ላይ ደካማ አፈጻጸም ያላቸው፣ ሥራ አቋርጠው የሄዱ ወይም በጥቁር መዝገብ (Backlisted) የተመዘገቡ ኮንትራከተሮች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ካልተገነዘበ ታይቶ ቢቀርብም እንኳ ውድቅ ይደረጋል። አንድ ተጫራች መግዛት የሚችለው አንድ የጨረታ ሰነድ ብቻ ነው።

6. የሰነድ አቀራረብ ሥርዓት - ተጫራቾች አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የቴክኒክ ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች፣ እንዲሁም አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የፋይናንሻል ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች በድምሩ ስድስት (6) ፖስታዎችን ለየብቻቸው በማሸግ፣ ሁሉንም መልሰው በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ (Outer Envelope) ውስጥ ከትተው በሰም በማሸግ ማቅረብ አለባቸው። በትልቁም ሆነ በትንንሾቹ ፖስታዎች ላይ የተወዳዳሪው ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና የፖስታው ዓይነት (ቴክኒክ/ፋይናንሻል) ተጽፎ ማኅተም ሊመታበት ይገባል። ሕጋዊ ሰነዶች በቴክኒክ ፖስታዎች ውስጥ መካተት ያለባቸው ሲሆን፣ የጨረታ ማስከበሪያው (CPO/ Bank Guarantee) ከዋናው (Original) ቴክኒክ ሰነድ ጋር መታሸግ አለበት።

7. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በኮርፖሬሽኑ የግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መግባት አለበት። የጨረታ ሳጥኑ በዚያኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይታሸጋል።

8. የቴክኒክ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ግምገማው በሁለት ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን፣ መጀመሪያ የቴክኒክ ብቃት የተረጋገጠላቸው ተጫራቾች የፋይናንሻል ሰነድ ቀጥሎ ይከፈታል)።

9. የማንኛውም ተጫራች የአርቲሜቲክ ስሌት ስህተት (Arithmetic Error) ማስተካከያ ውጤት ከጠቅላላው ዋጋ አንጻር ከ3% (ሦስት በመቶ) በላይ ሆኖ ከተገኘ ወይም የተደረገው ቅናሽ (Rebate) ከ10% በላይ ከሆነ ተጫራቹን ከጨረታ ውጭ ያደርገዋል።

10. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም።

አድራሻ እና ለበለጠ መረጃ፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (SE- IDPC) የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ስልክ
ቁጥር: +251 46 181 4411 / +251 46 181-4897 / +251 46 181 9175 / 09 16 71 07 90 ፖ.ሣ.ቁ 1814
አርባምንጭ፣ ኢትዮጵያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-04
  • Publishing entity: Southern Ethiopia Industry Park Development Cooperation
  • Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 13, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders