የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የዕንጨት ውጤቶች እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ/ቤ/ኮ/ብግጨ/ዕቃ/45/10/2018
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የዕንጨት ውጤቶች እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ክብ......ዕ/45/10/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
2. ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል የዕንጨት ውጤቶች እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ተጫራቾ የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸገ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
|
ተ.ቁ |
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የዕንጨት ውጤቶች እና ተዛማጅ እቃዎች |
100,000.00 |
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በፌደራል መንግስት ባለቤትነት የተያዙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1070/2017 መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው የእንጨት ውጤቶች እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀረ በሚገኘው ኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶራት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ኛው ወይም እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
6. የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011-855-36-17 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ዌብሳይት Website WWW.agh.gov.et
የፖ.ሣ.ቁ. PO Box 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-07-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-14 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jun 13, 2026
- Posted at: 2026-06-13T07:58:43.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.