የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ማስተካከያ አውጥቷል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ማስተካከያ

ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም ገጽ 31 ላይ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያ በስህተት የገቡ የእቃ አቅራቢዎች እና RC- 5 የሚባሉ ጸሁፎች በስህተት ከጨረታ ማስታወቂያው ውስጥ የገቡ በመሆኑ ከጨረታ ማስታወቂያው የወጡ መሆኑን እየገለጽን የተቀረው የጨረታ ማስታወቂያ በግንቦት 25 ቀን 2018ዓ/ም በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚቀጥል መሆኑን እንገልጻለን።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የኩታበር ወረዳ አስተዳደር ም/ቤት ላስገነባው የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስታንዳርዱን የጠበቀ መቀመጫ ወንበርና ሌሎች በአዳራሹ ውስጥ የሚገጣጠሙ እቃዎች ከደረጃ 5/አምስት/ በላይ የሆኑ ተቋራጮች (GC‐5 | BC‐5) ጠቅላላ ወይም የህንጻ ተቋራጮች ግዥ መፈጸምና ለማስገጠም ይፈልጋል።

Bid closing date

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት፣

Bid opening date

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት፣

ስለዚህ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋራጮች፡-

  1.  የኮንትራክተር ደረጃ መስፈርት በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ከደረጃ 5 አምስት እና በላይ በሆኑ ተቋራጮች (GC -5 / BC5) ጠቅላላ ወይም የህንጻ ተቋራጮች የሆኑ፣
  2.  የሚገዛው ወንበርና ሌሎች በአዳራሹ ውስጥ የሚገጣጠሙ እቃዎች በዲዛይኑና በሳንፕሉ መሰረት ግዥ ፈጽሞ ማቅረብ የሚችልና መግጠም የሚችል፣
  3.  በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በቴክኒካልና ፋይናሺያል በኦርጂናልና በኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
  5. የሚገዛውን የወንበርና ሌሎች በአዳራሹ ውስጥ የሚገጣጠሙ እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ::
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15/አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን ማግኝት ይቻላሉ፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሚያቀርበው ጠቅላላ እቃ ዋጋ 300,000/ሶስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው፡፡የኢንሹራንስ ቦንድ ወይም የግል ቼክ ተቀባይነት የለውም።
  8.  ጽ/ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ድምር ነው፣
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ነው።
  11. 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ጨረታው 5:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0334480228/0914054354/ 0914051585 በመደወል ማገኘት ይችላሉ።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር

ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

https://tender.2merkato.com/tenders/6a1fd6560a538aeefd000001 


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-17 11:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: South Wello Zone Kutaber Woreda FEDB
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 13, 2026
  • Posted at: 2026-06-13T08:30:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders