በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከል በማዕከሉ ውስጥ የዳቦና ኬክ ቤት ግንባታ ማካሄድ ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከል በማዕከሉ ውስጥ የዳቦና ኬክ ቤት ግንባታ ማካሄድ ይፈልጋል። 

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩና ደረጃቸው ደረጃ 7 (GC/ BC-7) እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላህንጻ ሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ህጋዊ መስፈርቶች፡-

1. በዘርፉ የተሰማሩ፣ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ 

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም ከገቢዎች ሚኒስቴር የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤

የጨረታ ሰነድ አገዛዝና አቀራረብ፦

  • ብቁ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ቄራ ሶፊያ ሞል ጀርባ በሚገኘው የወረዳ 06 ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ብቻ በግልፅ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ለ6 ቀናት የሚቆይ የባንክ ክፍያ ማዘዣ CPO ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ለብቻው በአንድ ፖስታ በማድረግ ከኦርጅናል ቴክኒክ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የቴክኒክ ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሺያል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ፣ በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። 

የጨረታው ማጠቃለያ ቀናት ሰንጠረዥ፦

ዝርዝር ተግባር

ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ሽያጭ የሚጀምርበት ቀን

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 የሥራ ቀናት አየር ላይ ይውላል።

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 09 ቀን እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ።

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

ዕለተ ረቡዕ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ አዳራሽ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፦ ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ እና ስልክ፦ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የወረዳ 06 ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከል፣ አዲስ አበባ። 

ስልክ ቁጥር፦ +251 91 445 2501 / +251 70 727 0851

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-06-16
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-06-17 09:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የወረዳ 06 ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከል
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 13, 2026
  • Posted at: 2026-06-13T08:59:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders