በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ.ም. ለከተማ አስተዳደሩ ቢሮ ግንባታ የሚሆኑ የግንባታ ማቴሪያል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ.ም ለከተማ አስተዳደሩ ቢሮ ግንባታ የሚሆኑ የግንባታ ማቴሪያል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፍርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ

3. የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው

4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው

5. የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና ከዚያም በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ NAT ከፋይነት የተመዘገበ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ 30,000/ ሰላሳ ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋት 3፡00 /ሶስት ሰዓት/ ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል።

ጨረታው በዚሁ ቀን 3፡31/ሶስት ከሰላሳ አንድ/ ተዘግቶ 4፡00 /አራት ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ውስጥ ይከፈታል።

8. የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፌኬሽን/ ክጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላል። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 የሰነድ ክፍያ በመፈጸም የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

10. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑ ይታወቃል።

11. የጨረታ ተሳታፊዎች ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ማህተም የሌላቸው ተጫራቾች ህጋዊ ፊርማችሁን ማስቀመጥ ይኖርባቸኋል።

12. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው።

13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ባዘጋጀዉ ሳይት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

በሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ከተማ
አስተዳደር ገንዘብ ጽ / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን 3፡31 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-29 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: በሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ / ቤት
  • Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T07:16:48.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders