የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ከብሔራዊ ዋሽ ኘሮግራም በተገኘ የበጀት ድጋፍ የውሃ መመርመሪያ ኪት በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ከብሔራዊ ዋሽ ኘሮግራም በተገኘ የበጀት ድጋፍ የውሃ መመርመሪያ ኪት በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ለመወዳደር የተጋበዙ መሆኑን እያሳወቅን ፡-

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርብ።

3. ከላይ በተራ ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።

4. የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት።

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ፤ ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ጠቅላ ዋጋ ከ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር) መብለጥ የለበትም።

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።

9. ሌሉች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

10. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

11. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሽነፈውን የውሃ መመርመሪያ ኪት የጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው አግባብ አብክመ ጤና ቢሮ ንብረት እስቶር ላይ ማቅረብ አለበት።

12, በጨረታው የተወዳደረ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር / በመክፈል ከቢሮው የሰነድ ሽያጭ ክፍል መውሰድ ይችላል።

13. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ስልክ ቁጥር 058-222-1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ 


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-29 15:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ9፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Health Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T08:17:16.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders