በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ የሚፈፀሙ ለታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ ግብዓት የሆነውን የትራንስፎርመር ኢናሜልድ ዋየር (diameter 1.5 mm and 1.8 mm) ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
1. በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ የሚፈፀሙ ለታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ ግብዓት የሆነውን የትራንስፎርመር ኢናሜልድ ዋየር (diameter 1.5 mm and 1.8 mm) ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል
3. በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
5.ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
6. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ አለበት
7. ተጫራቾች በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም በብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሎት -1 -የትራንስፎርመር ኢናሜልድ ዋየር (diameter 1.5 mm and 1.8 mm) 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
8. ተጫራቶች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለበት።
9. ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
10. ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢከፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ሰነዱን በሶፍት ኮፒ መግዛት ይችላሉ።
11. ተጫራቶች በገዙትና በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፁትን ሆኔታዎች በአግባቡ በመጠቀም የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12. ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ኤንቨሎፕ አሽገው 2ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
13. ተጫራች ለጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
14. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል። በዚሁም ዕለት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
15. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
16. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።
17. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን ስልከ: +251 92 495 5389 +251 91 016 2733 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
Tender details
- Deadline: 2026-06-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Bid opening: 2026-06-24 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Engineering Group Power Equipment Manufacturing Industry
- Buyer address: ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 14, 2026
- Posted at: 2026-06-15T10:56:16.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.