የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply of Combining Compartment Transformer ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/EM/93/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply of Combining Compartment Transformer ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን ከዚህ በታች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
Supply of Combining Compartment Transformer |
ቆሬ ዋር ኮሌጅ |
DCE/EM/ 93/2026 |
ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም 4:15 ሰዓት |
ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም 4:30 ሰዓት |
100,000.00 |
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ፣ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ... ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) ለ 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘውትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲሱ ቢሮ ቃሊቲ ቶታል ማድያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ ውስጥ
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን አንተርኘራይዝ የቀጥታ
ስልክ ቁጥር 0911 171 751 / 0913 297 297
E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ቃሊቲ ቶታል ማድያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-07-24
- Bid closing time: 10:15
- Bid opening: 2026-07-24 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Jul 15, 2026
- Posted at: 2026-07-15T08:58:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.