የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የአቅርቦት እና ገጠማ ሥራዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥሮች DCE/SF/82/2026 እና DCE/EM/83/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እና ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በዝርዝር የተጠቀሱትን የተለያዩ የአቅርቦት እና ገጠማ ሥራዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት
|
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
Supply & fix UPS
|
ፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
|
DCE/ SF/82/2026
|
ሰኔ 26/2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት
|
ሰኔ 26/2018 ዓ.ም 4፡45 ሰዓት
|
200,000.00
|
|
2 |
Supply of Combining Compartment Transformer
|
ቆሬ ዋር ኮሌጅ
|
DCE/ EM/83/2026
|
ሰኔ 26/2018 ዓ.ም 8:15 ሰዓት
|
ሰኔ 26/2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት
|
200,000.00
|
ስለሆነም:-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደለ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ...ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) መቅረብ ይኖርባቸዋል። የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲሱ ቢሮ ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ ውስጥ
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:-የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 09 11 17 17 51/ 09 13 29 72 97 E-mail አድራሻ info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ገቢ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-07-03
- Bid closing time: 14:15
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-03 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
- Bid bond: 200,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Jun 19, 2026
- Posted at: 2026-06-19T07:36:24.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.