የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸው የተጠናቀቀ 04 (አራት) ኮንደሚኒየም ሱቆች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ እና በ2019 በጀት ዓመት ለክርስትና እምነት ተከታዮች የዳልጋ ከብት ሥጋ መሸጫ ሱቆችን /ኮንቴይነሮችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኮንደምንም የንግድ ሱቅ ሽያጭ እና የሥጋ መሸጫ ሱቆች ኪራይ

ጨረታ ማስታወቂያ

Doc No:: አአቄድ/3.22

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸው የተጠናቀቀ 04 (አራት) ኮንደሚኒየም ሱቆች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ እና በ2019 በጀት ዓመት ለክርስትና እምነት ተከታዮች የዳልጋ ከብት ሥጋ መሸጫ ሱቆችን /ኮንቴይነሮችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-

  • ኮንደሚኒየሞቹ አዲስ አበባ በሚገኙ አራት ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ ሲሆኑ ያሉበት ሁኔታ እና የእያንዳንዱን የንግድ ሱቅ ስፋት ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይቻላል።
  • ለጋራ መኖሪያ ኮንደሚኒየም ንግድ ሱቅ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታ ቀን ድረስ የንግድ ሱቆች በሚገኙበት ሳይት በመገኝት ማየት ይቻላል።
  • ለዳልጋ ከብት ስጋ መሸጫ ሱቆች ኪራይ በተመለከተ በመስኩ ወይም በተመሳሳይ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑ ግብር የከፈለ የማይመለስ ኮፒ በማያያዝ ማቅረብ አለበት።
  • የጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ/ ለኮንደሚኒየም ሱቆች ሽያጭ ለእያንዳቸው ከተ.እ.ታ በፊት የሚገዛበትን ዋጋ 10% እና ለዳልጋ ከብት ስጋ መሸጫ ሱቅ ኪራይ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲፒኦ ገቢ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
  • የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለኮንደሚኒየም ሱቆች የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ እና የዳልጋ ከብት ሥጋ መሸጫ ሱቆች ኪራይ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  • የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎኘ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  • ጨረታው ለዳልጋ ከብት ሥጋ መሸጫ ሱቆች /ኮንቴይነሮች/ ኪራይ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 እና ለኮንደሚኒየም ሱቆች ሽያጭ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 4፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል።
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111 416 3978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-02
  • Bid closing time: 10:15
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-02 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Abattoirs Enterprise
  • Buyer TIN: 0000028921
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T12:01:38.000Z
  • Buyer website: https://www.aaae.gov.et/en/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders