ተስፋ ድርጅት ለሚያከናዉናቸዉ ተግባራት ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ ማቴሪያሎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ድርጅት በሲቭል ማህበራት ኤጄንሲ የተመዘገበ ህጋዊ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ሲዳማ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ሥልጠና እና በተለያዩ የልማት ሥራዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች አገልግሎት ይሰጣል:: ድርጅቱ ለሚያከናዉናቸዉ ተግባራት ግብዓት የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማቴሪያሎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
No |
Item |
Qty. |
|
1 |
Electric Vehicle battery Analyzer |
1 |
|
2 |
Electric Vehicle Diagnostic Scanner |
1 |
|
3 |
High Voltage insulation tester |
2 |
|
4 |
Electric Vehicle specification Diagnostic Tool |
1 |
|
5 |
Automotive Relay Tester |
1 |
|
6 |
Electric Vehicle Battery (One pack contains 9 pcs of batteries) |
1 |
|
7 |
Electrical Vehicle Charger Type2 |
1 |
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፊኬት ያለው።
2. የግብር መለያ ቁጥር (Tin No.) ሰርቲፊኬት
3. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን የዋጋ ሰነዶች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶኩመንት ለየብቻ በማሸግ ወይም ለየብቻ ያሸጉትን በአንድ ፖስታ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 5 የስራ ቀናት እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ድረስ አየር ጤና ተስፋ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (አምሣ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከቴክኒካል ዶኩመንቱ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8.00 ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ አየር ጤና ከሚገኘው ዋናው ቢሮ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ:: ዋጋ ማቅረብ የሚቻለው በተዘጋጀው ፎርም ብቻ ነው:: ማንኛዉም ስርዝ ድልዝ ተቀባይነት የለዉም።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ እስከ ማስረኪቢያ ቦታ (ተስፋ ድርጅት አየር ጤና ዋና መስሪያ ቤት ድረስ) ያለውን የትራንስፓርት ዋጋ ጭምር የያዘ መሆን አለበት።
8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
ስልከ ቁጥር 0113 694 480 / 0116 936 91
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-06-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-06-19 14:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hope Enterprise
- Buyer address: አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published: Jun 14, 2026
- Posted at: 2026-06-15T13:24:39.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.