ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የህትመት ውጤቶች ከቦታ ቦታ መጓጓዣ ጋሪ (ድርጅቱ ውስጥ በመገኘት የሚፈልገውን ሥራ አይቶ ዲዛይን ሠርቶ በማቅረብ የወረቀት ማጓጓዣ ጋሪዎቹን መሥራት) አገልግሎት ግዥ፣ ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የሆነ (Fully Automatic all in one machine) ወይም ጥሬ ዕቃ በመጠቀም እስከ ማንጠልጠያ ገጠማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 016/18
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
- በጨረታ አንድ (ሎት 1) - የህትመት ውጤቶች ከቦታ ቦታ መጓጓዣ ጋሪ (ድርጅቱ ውስጥ በመገኘት የሚፈልገውን ሥራ አይቶ ዲዛይን ሠርቶ በማቅረብ የወረቀት ማጓጓዣ ጋሪዎቹን መሥራት) አገልግሎት ግዥ፣
- በጨረታ ሁለት (ሎት 2) - ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የሆነ (Fully Automatic all in one machine) ወይም ጥሬ ዕቃ በመጠቀም እስከ ማንጠልጠያ ገጠማ
በአንድ ላይ የሚሠራ የወረቀትና የጨርቅ ከረጢት (Bag) መሥሪያ ማሽን ብዛት 1. ግዥ፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስስሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ሕንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
ጨረታው 7/11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር 011-155-5230 ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-07-14
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-07-14 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Berhanena Selam Printing Enterprise
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 15, 2026
- Posted at: 2026-06-16T07:40:04.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.