በማዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ የስልጤ ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሼድ ግንባታ በዘርፉ የተደራጁ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ የስልጤ ፈይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሼድ ግንባታ በዘርፉ የተደራጁ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ደረጃቸው GC/B.C-9 የሆኑ ማህበራት

  • የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ ፣
  • የታደሰ የንግድ ፍቃድና የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የጨረታ ዋስትና 20,000 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ የሚችሉ፣
  • የስራ ልምድ ሁለት ስራዎች እያንዳንዳቸው የውል ዋጋ አንድ ሚልየን ብር ያለነሱ፣
  1. አጠቃላይ የስራ ልምድ አንድ ፕሮጀክት የውል ዋጋ አንድ ሚልዮን ብር፣
  2. ተዛማጅ ያስራ ልምድ አንድ ፕሮጄክት የውል ዋጋ አንድ ሚልዮን ብር፣

ማህበራት ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በማቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፣ የጨረታ ሰነዱ ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን 8፡ዐዐ ሰዓት ታሽጎ ከ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።10ኛው ቀን የስራቀን ከልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል።
  • የተወዳዳሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጡም።
  • ለስራ ልምድ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች 1. ውል 2. የመልካም ስራ አፈጻጸም ደብዳቤና 3. የክፍያ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  • መምሪያው የተሻለ አማራጭ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • እጃቸው ላይ ሁለትና ከዛ በላይ ፕሮጀክቶች ኖሮ አፈጻጸሙ ከ70 በመቶ በታች ከሆነ ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 046 771 0586 ደውሎ ወይንም ስ/ዞ/ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁ 3 ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።

የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Publishing entity: ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders