የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት በአምዋጭ ስደተኛ ሳይት ዳባት ከተማ እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት ገንደውሃ ከተማ በሚገኘው በስደተኛ ሳይቱ መጋዘን የሚገኘውን ሲሚንቶ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የስሚንቶ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ለተአ/ዳባት/001/2018
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት በአምዋጭ ስደተኛ ሳይት ዳባት ከተማ እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት ገንደውሃ ከተማ በሚገኘው በስደተኛ ሳይቱ መጋዘን የሚገኘውን ሲሚንቶ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በጎንደር ቅ/ፅ/ቤት እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ ቤት ቅጥር ግቢ አስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ከፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሰኔ 08 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3) ማንኛውም ተጫራች ከሰኔ 08 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት እና ገንደውሃ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም።
4) ጨረታው ጎንደር ከተማ አምባራንስ ሆቴል በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሰኔ 19 ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያሰያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያለያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
6) ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 91 387 1445 ወይም +251 91 004 8505 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 13:30
- Bid opening: 2026-06-26 14:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Refugee and Returnee Service Gondar Office
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 15, 2026
- Posted at: 2026-06-16T08:08:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.