ጣና ፍሎራ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በእጅ የሚገፋ ትራክተር በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
Description
በእጅ የሚገፋ ትራክተር ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ በ124 ሄክታር ላይ በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን ለእርሻ ልማቱ አገልግሎት የሚውል በእጅ የሚገፋ ትራክተር በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ኩባንያው ተጫራቾችን ይጋብዛል።
- Super DI power tiler hand working tracter_model DI 120
- 12 hp
- rpm 2000
- cc 744
- total weight 502kg
- full tanker capacity 10.7 L
- model Dl 120 ተጨማሪ ስፔሲፊኬሽኖችን በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ያገኙታል።
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናበር/ ያላቸው።
2. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
3. የተ. እታ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ቅጹን) የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከኩባያው ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 004 መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በመገኘት የዋጋ ማቅረቢያ ቅጹን መውሰድ ይችላሉ።
7. ጨረታው ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ታሽጎ በባህር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 48 15 98/ 09 13 69 63 83 ወይም 058 220 4798 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
9. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
10. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ድረስ በመቅረብ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12. ኩባንያው ውሉን እንደየአስፈላጊነቱ በየስድስት ወሩ ሊያድስ ይችላል።
13. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ: ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ኃይሌ ት/ቤት ጐን ስልክ ቁጥር 058 220 4798 ኢሜል፡ tanaflorapum@gmail.com tanaflorgm@gmail.com
ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30
- Bid opening: 2026-07-03 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Tana Flora P.L.C.
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jun 16, 2026
- Posted at: 2026-06-16T08:31:37.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.