የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃ/ማ/ጣቢያ የኬሚካል ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/09/2018

  • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃ/ማ/ጣቢያ የኬሚካል ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
  • ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 1ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ የቢሮ ቁጥር 114 መውሰድ ይችላሉ።
  •  ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የኬሚካል ግዥ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/09/2018 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 2(ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ) ለ60(ስልሳ) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ አለባቸው።
  • ጨረታው ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ቢሮ ይከፈታል።
  • ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 40 12 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-06-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-25 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: 120,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published: Jun 16, 2026
  • Posted at: 2026-06-16T09:12:02.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders