በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ የዕቃና አገልግሎት ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ የዕቃና አገልግሎት ግዥዎችን ማለትም -

1. ሎት - 1 የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ

2. ሎት - 2 የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት

3. ሎት - 3 የተሽከርካሪ ኢንሹራንስና እንዲሁም

4. ሎት - 4 የመንግስት ሠራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የኮንትራት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

ስለሆነም ፡-

1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin /ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ ፤

3. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /Vat/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1 እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የግዥ ፈጻሚ መ/ቤቱ ከቫት ከፍያ ላይ 7.5% እና የዊዝ ሆልዲንግ 3% ከጠቅላላ ክፍያ ላይ ቀንሶ የሚያስቀር ሲሆን በተጨማሪም የግዥ ፍላጎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 / ሦስት መቶ ብር ብቻ / በግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በመቅረብና በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት፣ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 / ሃምሣ ሺህ ብር / እና የተሽከርካሪ ጥገናና ሰርቪስ እንዲሁም የመንግስት ሠራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ ብር 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር / በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሲፒኦ (CPO) ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገው በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 22 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡01 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል።

10. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች የዕቃና አገልግሎት ግዥው በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የፑል አገልግሎት ለሚያገኙት ተቋማት በኮንትራት ውል ተይዞ የሚፈጸም ግዥ በመሆኑ ተጫራቾች በደ/ብርሃን ከተማ የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቅርንጫፍ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

11. የጨረታ መክፈቻው ዕለት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር22 ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 011- 681-32-41 ወይም 011-681-63-96 በመደወል መጠየቅና መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ

ደ/ብርሃን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡01 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-01 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shoa Zone Finance Department
  • Buyer address: Deberberhan, Amhara
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published: Jun 16, 2026
  • Posted at: 2026-06-16T09:49:41.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders