መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን የዱቄት ማበልጸጊያ ማሽን ግዥ እንዲሁም በቆሎ፣ ጤፍ እና ሩዝ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.
- ሎት 1. በቆሎ ሽያጭ፣
- ሎት 2. ጤፍ ሸያጭ፣
- ሎት 3. ሩዝ ሽያጭ እንዲሁም
- ሎት 4. የዱቄት ማበልጸጊያ ማሽን ግዥ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ብቻ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ዋስትና) ወይም (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙን ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ዋጋ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ክብ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በፖስታው ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሀምሳ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚቆየው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል፡፡
- ቅዳሜ ለዩኒየኑ የሥራ ቀን ቢሆንም ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን የንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ከሎት አንድ ወጭ ያሉትን ግን ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ያሸነፈዉን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ የሚያቀርብ ሲሆን ማንኛዉም ወጭ አሸናፊዉ ይሸፍናል፡፡
- የሚገዙትን ሆነ የሚሽጡ ማንኛዉም እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየዉ በተናጠል ይሆናል፡፡
- አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ግዥዎች /ሽያጭ/ በፍትህ ዉሉ ከተመረመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊዉ ይከፍላል፡፡ ሰብሉን ለማንሳት የሚያሰፈለጉ ማንኛውም የወዛደር ማስጫኛ እና የትራንሰፓርት ወጭዎች አሽናፊ የሚሽፍን ይሆናል፡፡
- ሰብሉ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዘን ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት ይችላሉ፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 11 55 36 53 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
- Bid opening: 2026-06-25 14:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Merekeb Farmers' Cooperative Union
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 350 (ሶስት መቶ ሀምሳ ብር)
- Published: Jun 15, 2026
- Posted at: 2026-06-16T11:27:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.