Fresh produce, meat and dairy

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሀዋሳ ኤርፖርት ፓይለት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት (PTSC) ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የስጋ ምርት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት ለመሥራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: SSNT-T622

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሀዋሳ ኤርፖርት ፓይለት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት (PTSC) ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የስጋ ምርት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት ለመሥራት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

በአገልግሎቱ ዘርፍ ለመሠማራት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፊቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ ሁለት (2) ዓመትና እና ከዚያ በላይ የሠራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT T622 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Ship Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሀምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እና የጨረታ ማስከበሪያ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ሀምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552

አሊ አስፋው

ኢ-ሜይል: [email protected]

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-17
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-07-17 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Jun 17, 2026)
  • Posted at: 2026-06-17T07:47:52.000Z
← Back to all tenders