የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለባቡር እና ለባቡር መሰረተ-ልማት ጥገና የሚዉሉ የመለዋወጫ መሣሪያዎች አላቂ እቃዎች፤ ዘይት እና ግሪስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር፦ 004/2018 ለባቡር እና ለባቡር መሰረተ-ልማት ጥገና የሚዉሉ የመለዋወጫ መሣሪያዎች አላቂ እቃዎች፤ ዘይት እና ግሪስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበረያ |
|
ሎት 1 |
ለጥገና አገልግሎት የሚዉሉ መሣሪያዎች ግዥ |
150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር) |
|
ሎት 2 |
ለጥገና አገልግሎት የሚዉሉ መለዋወጫዎች |
150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር) |
|
ሎት 3 |
ለጥገና አገልግሎት የሚዉሉ አላቂ እቃዎች ግዥ |
70,000 (ሰባ ሺህ ብር) |
|
ሎት 4 |
ለጥገና አገልግሎት የሚዉሉ ዘይት እና ግሪስ ግዥ |
70,000 (ሰባ ሺህ ብር) |
1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው እና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin No /ያላቸው
5. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም የተዘጋጀ CPO እና የተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ ማሰራት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን CPO በተቀመጠዉ ሎት መሰረትያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት በሪፖርተር ጋዜጣ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል።
7. ማንኛውም ተጫራች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ) በድርጅቱ ስም በተከፈት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000493811049 በመክፍል ያስገቡበትን ዲፖዚት ስሊፕ ይዘዉ በመምጣት ዘውትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት መግዛት ይችላሉ።
8. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ ካላቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
9. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ አሽገው የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
10. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፣
11. ጥቃቅንና አንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸዉ ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ
ሀ. ከደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለበት
ለ. ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ በመመሪያ መሰረት ለምትወደደሩበት ዕቃ አምራች መሆን አለባቸሁ
12. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝር ላይ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል። እንዲሁም አሸናፋው የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት ይህ ባይሆን ግን ለዋስትና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
13. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኝው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 24/2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
14. ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 24/2018 ዓም ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆናል።
15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 470 8116
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-01 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Light Rail Transport Service Enterprise (AALRTSE)
- Buyer address: Addis Ababa Light Rail Transit Service(Kality Depot) 1st Floor
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 17, 2026
- Posted at: 2026-06-17T08:11:58.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.