ፀደይ ባንክ አ.ማ. ባህርዳር ዋና መ/ቤት ህንፃ እድሳት እና የጥገና ስራ እና በደብረታቦር ዲስትሪክት የአለቃ ገብረሃና ቅርንጫፍ የማስፋፊያ ግንባታ ስራ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል
Description
ፀደይ ባንክ አማ Tsedey Bank (S.C)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0019/2018
ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች /ስራዎች /አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል።
|
ሎት 1 |
ባህርዳር ዋና መ/ቤት ህንፃ እድሳት እና የጥገና ስራ |
|
ሎት 2 |
በደብረታቦር ዲስትሪክት የአለቃ ገብረሃና ቅርንጫፍ የማስፋፊያ ግንባታ ስራ |
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5 እና በላይ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5 እና በላይ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
- የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ # የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት # በጨረታ ለመካፈል ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት። ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ / CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር 500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ
በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ስልክ ቁጥር
011 558 1658
ፀደይ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-01 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Jun 17, 2026
- Posted at: 2026-06-17T08:56:10.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.