Tyres, batteries and consumables

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሐዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በኩል ለ2018 ዓ/ም በመደበኛ እና በፕሮግራም በጀት ለ2018 የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በኩል ለ2018 ዓ/ም በመደበኛ እና በፕሮግራም በጀት ለ2018 የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

1ኛ. በዘርፉ የታደሰ የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ህጋዊ ፍቃድ ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፦

2ኛ. የንግድ ስራ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፦

3ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወርቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፦

4ኛ. የቲን ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል

5ኛ. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል

6ኛ. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ (ስም በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000454620918 ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫይስ በመያዝ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ግዥ/ክ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት መውሰድ ይቻላል።

7ኛ. ተጫራቾቸ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር (cpo) ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው 60,000.00/ ስልሳ ሺህ ብር / በባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15ኛ ቀናት እስከ 11:30 ድረስ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ ግዥ/ክ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።

9ኛ. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው 16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ4:00 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 የጨረታ ሳጥን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግ/ክ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል።

10ኛ የጨረታ መዝጊያ ወይም መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት እና ቀን ይሆናል።

11ኛ. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።

12ኛ. አሸናፊ ድርጀት ዕቃዎችን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ ቦንጋ ማቅረብ የሚችል

13ኛ. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 331 1723 እና 047 899 1601 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት ግብርና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ4:00
  • Bid opening: 2026-07-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: South West Ethiopia Peoples Regional State Agriculture Bureau
  • Bid bond: 60,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jun 17, 2026)
  • Posted at: 2026-06-17T09:06:24.000Z
← Back to all tenders