በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተተው ዕቃዎች የሐራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ_42/2018 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸዉን በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመዉ ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተዉ የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣዉ የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን ማለትም  LADY SKIRT, LADY TROUSER, LADY TIGHT, LADY SPORT SHOES & OTHER, PERFUME, BLANKET & OTHER, ASBESTOS FREE CLUTCH FACING, LABORATORY STOOL CHAIR, VIBRATION ANALYSIS OF CENTERFUGAL BLOWER FAN, HAIR CLIPPER, WACUUM FLASK, CHEWING GUM & OTHER፡ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ሺቲዎችና ሌሎች እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት  ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 ድረስ ከሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገቢ ሂሳቦች ቡድን መግዛት ይቻላል።

2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆነ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርጫፎች ብቻ መዘጋጀት አለበት።

4. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ6ኛው ቀን ከጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

5. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

6. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPOያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

7. በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

8. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-9094 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-23
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ6ኛው ቀን ከጠዋት 4፡45 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-23 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ6ኛው ቀን ከጠዋት 5፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian's Customs Commission Modjo Branch Office
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Published: Jun 17, 2026
  • Posted at: 2026-06-17T09:15:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders