የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የብረታ ብረት ውጤቶች እና የማሽን እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕቃ/46/10/2018

1. የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የብረታ ብረት ውጤቶች እና የማሽን እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕቃ/46/10/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

2. ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል የዕንጨት ውጤቶች እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።

.

የዕቃ ዝርዝር

የጨረታ ማስከበሪያ

1

የብረታ ብረት ውጤቶች እና የማሽን እቃዎች

150,000.00

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በፌደራል መንግስት ባለቤትነት የተያዙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1070/2017 መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው የብረታ ብረት ውጤቶች እና የማሽን እቃዎች ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።

4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀረ በሚገኘው ኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ኛው ወይም እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬከተር 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

6. የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 011-855-36-17 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዌብሳይት/ Website WWW.agh.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ. P.O. Box 299

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-21 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Housing Corporation
  • Bid bond: 150,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 18, 2026
  • Posted at: 2026-06-18T07:56:31.000Z
  • Buyer website: https://www.fhc.gov.et

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders