የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት ለወ/ሮ እመቤት ስዩም ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተበዳሪው የመያዣ ሰጪው/ስም |
የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
የሐራጁ መነሻ ዋጋ |
የሐራጁ ደረጃ |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ እና ቀን ሰዓት |
|
ወ/ሮ እመቤት ስዩም የወንዶች ልብስ ስፌት |
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ቀበሌ 10 ውስጥ በ876 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ ዲጂታል የልብስ ስፌት ማሽኖች፣ ጥሬ ዕቃዎችና ያለቀለት የጨርቅ ውጤቶች እና የቢሮ ዕቃዎችና ቁሶች |
61,041,737.69
|
1ኛ
|
በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከ4፡30-6፡30 ሰዓት
|
ማሳሰቢያ፡-
1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ ለባንኩ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪ ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ በሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
3. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።
4. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
5. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
6. የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስVAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
7. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተወካዮች ብቻ ናቸው።
8. ከፕሮጀክቱ ጠቅላላ ይዞታ 1.8 ሜትር ለኮርደር ልማት በአሰላ ከተማ መስተዳደር የሚቀነስ መሆኑ እና ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-211-66-87 ላይ መደወል ይችላሉ።
9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሃራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሐራጁ አይገደድም።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-07-20
- Bid closing time: 12:30
- Bid opening: 2026-07-20 12:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 18, 2026
- Posted at: 2026-06-18T08:03:43.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.