በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተተዉ ዕቃዎች ግልጽ ጨረታ ግ_37/2018 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተው ንብረቶችን CHIFFON MATERIAL: VELVET FABRIC SOFA MATERIAL: CAUSTIC SODA FLAKES AS MEN SPORT SHOES, MEN SHIRT, CASTOR OIL, HAIR CLIPPER, MEN TROUSER SHITY, DIFFERENT TYPE OF PERFUMES & OTHERS እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ ዓይነት፣ ብዛት፤ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው:: ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHOPIAN CUSTOMS COMMSSON MOD]O BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት። ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አሰቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም። በጨረታ ተሽጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፣ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም።

5. የግልጽ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፤ የሞሉበት ሠነድ፤ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል። የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም::

7. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌሎች ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፤ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

8. የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።

9. በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

10. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው። በጨረታ ተሽጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም::

12 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45
  • Bid opening: 2026-06-26 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀን አልተገለፀም
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian's Customs Commission Modjo Branch Office
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Jun 18, 2026
  • Posted at: 2026-06-18T11:02:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders