በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ኤ/አገ/ቤት ፅ/ቤት የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ስካነር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ግዥጨረታማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ወ/ሪጅ/ግጨ/004/2018

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ኤ/አገ/ቤት ፅ/ቤት ከዚህ በታች የተገለፁትን የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ስካነር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን

ሎት 1

አላቂ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች

92,437.00 /ዘጠና ሁለት ሽህ  አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ብር ብቻ/

ሰኔ 22 ቀን 2018 .ም ጠዋቱ 430

ሎት 2

የፕሪንተር ቀለሞች

24,545.60 (ሃያ አራት ሽህ አምስት መቶ አርባ አምስት ብር 60/100)

ሰኔ 22 ቀን 2018 .ጠዋቱ 430

ሎት 3

የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መጠቀሚያ ማሽኖች (ኮምፒዩተር ስካነር ፕሪንተር ፎቶ ኮፒ እና ኤለክትሮኒክስ…)

241,910.00/ሁለት መቶ አርባ አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ አስር ብር ብቻ /

 

ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓም ከቀኑ 1030

 

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ እና ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin No/ ያላቸው
  3. የመንግሥት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ እና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት በፖስታ አሽገው ሲመጡ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና ተያያዥ መረጃዎች የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል ባለበት ፖስታ ውስጥ በማስገባት እና በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ወልዲያ ሪጅን ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ለሎት አንድ ብር 92,437.00 /ዘጠና ሁለት ሽህ አራት መቶ ሠላሳ ሰባት ብር ብቻ/፣ ለሎት 2 ብር 24,545.60 (ሃያ አራት ሽህ አምስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ60/100 ብቻ )፤ ለሎት 3 241,910.00/ሁለት መቶ አርባ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አስር ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር መቅረብ አለበት።
  7. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ሳምፕል የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካል አሪጅናል እና ኮፒ እና ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በ4 በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ኢ/ኤ/አገ/ወ/ ሪጅ/ ጨ/004/2018 የሚል ምልክት በማድረግ ለሎት1 እና 2 ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለሎት 3 ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓም ከቀኑ 10፡00 ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 15 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለሎት 1 እና 2 ከጠዋቱ 4፡30 ለሎት 3 ከቀኑ 10፡30 ከሰዓት ላይ ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033-431 88-20 መደወል ይችላሉ።
  11. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ኤ/አገ/ቤት ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-06-29 16:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: Jun 19, 2026
  • Posted at: 2026-06-19T08:14:53.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders