አድህኖ የተቀናጀ የገጠር ልማት ማህበር በሰሜን ሸዋ ዞን በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በልቼ ቀበሌ አስተዳደር ስር በሚገኘው የዛንጅራ የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለ አራት የመማሪያ ክፍሎች ያለው አንድ ህንፃ (ብሎክ) በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
አድህኖ የተቀናጀ የገጠር ልማት ማህበር በሰሜን ሸዋ ዞን በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በልቼ ቀበሌ አስተዳደር ስር በሚገኘው የዛንጅራ የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለ አራት የመማሪያ ክፍሎች ያለው አንድ ህንፃ (ብሎክ) በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- በት/ቤት ግንባታ ልምድ ያለውና ደረጃው 7 እና ከ7 በላይ የሆነ፤
- የግንባታ ሥራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ፤ የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ፤ ቫትና ቲን ሰርተፌኬት ማቅረብ የሚችል ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርብ፤
- በአማራ ክልል ት/ቢሮ የመማሪያ ክፍሎች የግንባታ ደረጃ (ስታንዳርድ) የመገንባት ልምድ ያለው፤
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ አድህኖ የተቀናጀ የገጠር ልማት ማህበር ዋና መ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ገዝታችሁ የሥራ ዝርዝሩን ሰነድ ኦሪጂናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ትችላላችሁ።
- የጽ/ቤቱ አድራሻ፡- አዲስ አበባ፤ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ጎዳና ከኡራኤል ቤተክርስቲያን ወረድ ሲሉ ባለው ፕላዛ ሆቴል 100 ሜትር ገባ ብሎ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 504 2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።
- ጨረታው የሚቆይበት ወቅት፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት፡
- የጨረታ ሰነዱ ዋጋ 1000.00 (አንድ ሺ ብር ብቻ)
- ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዣ ለጨረታ ካስገቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2% (ሁለት ከመቶ) ያላነሰ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ማህበሩ ሌላ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በተዘጋ በቀጣይ የሥራ ቀን 4፡00 ሠዓት ላይ ይሆናል።
- ቦታው በድርጅቱ ጽ/ቤት ስለሆነ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይኖርባቸዋል፤
- ሕንጻውን የሚያስረክቡበት ቀን፡ አሸናፊው ውሉን ከፈረመበት ቀን ጀምሮ በሁለት ወር ማስረከብ ይኖርበታል።
ለበለጠ መረጃ፡ 0911 169 341 ወይም 0912 634 184
አድህኖ የተቀናጀ የገጠር ልማት ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-06-26 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በቀጣዩ የሥራ ቀን 4፡00 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Adehano Integrated Rural Development Association
- Buyer address: ከኡራኤል ቤ/ክ/ወረድ ሲሉ በሚገኘው ፕላዛ ሆቴል ወደ 100 ሜትር ገባ ብሎ በስተግራ ቀይ ቡኒ ቀለም የተቀባ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: Jun 20, 2026
- Posted at: 2026-06-20T07:43:52.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.