የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት Ready mix concrete with Pump እና አልሙኒየም ፕሮፋይሎች ከነአክሰሰሪው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 24/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 Ready mix concrete with Pump
- ሎት 2 አልሙኒየም ፕሮፋይሎች ከነአክሰሰሪው
ስለሆነም፡-
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመከፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማስልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት-1 ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለሎት-2 ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ለሎት 1 ከረፋዱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5፡00 የሚከፈት ሲሆን ለሎት 2 ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 09-13-56-49-36
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-30
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-30 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
- Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 20, 2026
- Posted at: 2026-06-20T07:46:31.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.