በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የነቀምት ሪጅን ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12*20፣ የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ 7.50*16፤ 8.50*16 እና የኒሳን ደብል ጋቢና ቲዩብለስ ጎማ ከነ ሙሉ አክሰሰሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12*20 ፣ የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ 7.50*16፤8.50*16 እና የኒሳን ደብል ጋቢና ቲዩብስስ ጎማ ከነ ሙሉ አክሰሰሪ ግዥ ለመፈጸም የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EEU/NREU/NCB/09/2018

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የነቀምት ሪጅን ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12*20 ፣ የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ 7.50*16፤ 8.50*16 እና የኒሳን ደብል ጋቢና ቲዩብለስ ጎማ ከነ ሙሉ አክሰሰሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፤

በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስክ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ https://epg.ppa.gov.et ድረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2. የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ ም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 300 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ EEU Nekemt region ተከፋይ የሆነ የካባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12*20 ከነሙሉ አክሰሰሪ ብር 70.000.00 (ሰባ ሺህ ብር) እና ለቀላል ተሽከርካሪ ጎማ 7.50*16 ጎማ ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሽገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ እንዲሁም ፋይናንሻል ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ ሲፒኦ /CPO/ ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ በመክተት አራቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን ነቀምት ከተማ ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እጠገብ በሚገኘው ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 300 በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል።

6. ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0576602015/0911570832/0911564806 መጠየቅ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የነቀምት ሪጅን ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-02
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-02 14:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Oromia Region Electric Utility Nekemite District
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 20, 2026
  • Posted at: 2026-06-20T08:17:10.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders